=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
አሏህ ምንም ነገር አይወስድብህም የተሻለ ነገር የሚተካልህ ቢሆን እንጂ። ያ ግን የሚሆነው ከታገስክና ምንዳን ከከጀልክ ነው። «ሁለቱን ውድ ዐይኖቹን ወስጄበት የታገሰ ሰው በጀነት እክሰዋለሁ።» ልጁን አጥቶ የታገሰ ሰው ጀነት ውስጥ በይተል ሐምድ (የምስጋና ቤት ) ይገነባለታል። ሌሎችም መከራዎች በዚሁ መልክ ይመነዳሉ።
በደረሰብህ መከራ አትዘን ምክኒያቱም እንዲደርስብህ የቀደራት አሏህ እርሱ ዘንድ ጀነት ፣ ካሳና ታላቅ ምንዳ አለና። ፈተናና መከራ የተፈራረቀባቸው የአሏህ ወዳጆች በፊርደውስ ውስጥ እንዲህ ይባላሉ:-
-<({አል-ቁርአን 13:24})>-
«ሰላም ለናንተ ይሁን ይህ ምንዳ በመታገሳችሁ ነው። የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር።»
አንድን መከራ ተከትሎ የመጣውን ምንዳ ፣ መልካም ነገር እና መካሻ በቅጡ መገንዘብ ይገባናል።
-<({አል-ቁርአን 2:157})>-
«እነዚያ በነርሱ ላይ ከጌታቸው የኾኑ ችሮታዎችም ምህረትም አለ። እነርሱም ወደ እውነት ተመሪዎች ናቸው።»
የምስራች ለተጐጅዎችና ለመከራ ቀማሾች። ዱንያ እድሜዋ አጭር ነው። ብልጭልጭ ነገሯም ወራዳ ነው። አኺራ የተሻለ ፣ ዘውተሪና ዘላለማዊ ነው። ስለዚህ እዚህ የተጐዳ እዚያ ይካሳል። እዚህ የደከመ እዚያ ያርፋል። በዱንያ ላይ የተንጠለጠሉ ዱንያን ያፈቀሯት ፣ የተመኩባት ልቦቻቸው የሚሰበሩበትና እጅጉን የሚቆጩበት አንድን ዱንያዊ ጥቅም ሲያጡ እና አንዳች እረፍት የሚነሳ ነገር ሲገጥማቸው ነው። ያም እሷን ዱንያን ብቻ ስለሚሹ ነው። ለዚህም ነው ችግሮችን መቇቇም እጅጉን የሚከብዳቸው፤ መከራዎችም የሚገዝፉባቸው። ምክኒያቱም እግራቸው ስር ሲመለከቱ አላቂዋ እና ርካሿ ዱንያ እንጂ ሌላ አይታያቸውም።
ችግሮች የደረሱባችሁ ሰዎች ሆይ ምንም ቢያመልጣችሁ ትርፋሞች ናችሁ። በመስመሮቹ መካከል ርህራሄ ፣ እዝነት ፣ ምንዳና ትክክለኛ ምርጫ ያለበት ደብዳቤ ተልኮላቸዋል። መከራ የተፈራረቀበት ሰው ውጤቶቹን አጢኖ መመልከት ይኖርበታል። እንዲህም ሆኖ ያገኘዋል:-
-<({አል-ቁርአን 57:13})>-
«በመካከላቸውም ለርሱ ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል ግቢው በውስጡ ችሮታ ገነት ያለበት ውጩም ከበኩሉ ስቃይ እሳት አለበት።»
አሏህ ዘንድ ያለው ግን መልካም ፣ ዘውታሪ ፣ የተሻለ ፣ አስደሳችና የላቀ ነው።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
|
---|